ድንገተኛ ክስተቶች (Emergencies)

 • በተደጋጋሚ የሚቀርቡ ጥያቄዎች የአየር ንብረት ማስጠንቀቂያና የድንገተኛ ሁኔታዎች ማስታወቂያዎች (PDF)

  በከባድ የአየር ጸባይ አማካኝነት ትምህርት ቤት ሲዘጋ በሚከተሉት መንገዶች ይፋ ይደረጋል፦

  በሌሎች ድንገተኛ ክስተቶች ወቅት መረጃው በተቻለ ፍጥነት በቶሎ ይፋ ይደረጋል። ወላጆች ለልጆቻቸው ጥበቃ ማዘጋጀት አለባቸው።

  ትምህርት ቤቶች ለሙሉ ቀን በሚዘጉበት ወቅት በእለቱ ሊደረጉ ታሰበው የነበሩ ከትምህርት በኋላ እንቅስቃሴዎች እና የስፖርት ዝግጅቶች በሙሉ ይሰረዛሉ።

  የፌዴራል ወይም የአሌክሳንድሪያ መንግስታዊ መስሪያ ቤቶች መዘጋት ወይም መከፈት የትምህርት ቤቶች መከፈት እና መዘጋትን አያስከትልም።

  የACPS የኮሚኒኬሽን ቢሮ ሁሉንም ከድንገተኛ ክስተቶች ጋር ተዛማጅ የሆኑትን መረጃዎች ያስተባብራል። አስቸኳይ ጊዜ ክስተቶች በሚያጋጥሙበት ወቅት የኮሚኒኬሽን አገልግሎት በትምህርት ቤቶች እና በህዝብ/በሚዲያ መካከል አገናኝ ሆኖ ይሰራል።


  የድንገተኛ ጊዜ መዘጋት/መዘግየት አሰራሮች፦

  ሁለት ሰዓት ዘግይቶ መከፈት

  ተማሪዎች፦

  ከመዎዕለ ህፃናት እስከ 12 ክፍል እንዲሁም የቨርጂኒያ ቅድመ መደበኛ ትምህርት መርሃግብር (VPI) ተማሪዎች ከመደበኛው የትምህርት ሰዓት ሁለት ሰዓት ዘግይተው ይጀምራሉ።

  የጥዎት ቅድመ መዎዕለ ህፃናት ፕሮግራሞች (የቅድመ ሕፃናት ልዩ ትምህርትና ቅድመ መደበኛ ትምህርት በጋራ የሚከታተሉ ተማሪዎች።)(Early Childhood Special Education and Preschoolers Learning Together) ከመደበኛው የትምህርት ሰዓት ሁለት ሰዓት ዘግይተው የሚጀምሩ ሲሆን ከተለመደው መውጫ አንድ ሰዓት ዘግይተው ይወጣሉ። የከሰዓት በኃላ ቅድመ መዎዕለ ህፃናት አንድ ሰዓት ዘግይተው በመግባት በመደበኛው የመውጫ ሰዓት ይወጣሉ።

  ሰራተኞች፦

  ሌሎች ስራተኞች ከመደኛው የስራ መግቢያ ሁለት ሰዓት ዘግይተው ይገባሉ።

  ለማስተማሩ ስራ አስፈላጊ የሆኑ ሰራተኞች በመደበኛው የስራ ሰዓት ይገባሉ።


  አንድ እና ሁለት ሰዓት ቀድሞ መዘጋት

  ተማሪዎች፦

  ሁሉም ትምህርት ቤቶች በሚገለጸው መሰረት ከአንድ ወይም ከሁለት ሰዓት በፊት ይለቀቃሉ። ትምህርት ቀድሞ ሲዘጋ የማካካሻ ክፍለ ጊዜዎች አይጠየቁም።

  የጠዋት ቅድመ ትምህርት ቤት/ፕሪ-ስኩል ተማሪዎቸች 11:00 a.m. ላይ ያለቀቃሉ። የከሰዓት ቅድመ ትምህርት/ፕሪ-ስኩል ይሰረዛል (ማካካሻ ክፍለ ጊዜዎች ሊያስፈልግ ይችላል)።

  ሰራተኞች፦

  አስተዳዳራዊ ያልሆኑ ፈቃድ ያላቸው ሰራተኞች፣ ከፊል ባለሞያዎች እና የአዳራሾች ተቆጣጣሪዎች ተማሪዎች ከተለቀቁ እና ሁሉም አውቶቡሶች ከትምህርት ቤቱ ከወጡ በኋላ በርዕሰ መምህሩ ውሳኔ ሊለቀቁ ይችላሉ።

  ሁሉም ሌሎች ሰራተኞች በመደበኛው ሰዓት እንዲሰሩ ይጠበቃል።

  የማታ ሰራተኞች በመደበኛ ሰዓት ሪፖርት ማድረግ አለባቸው ወይም በተቆጣጣሪያቸው ውሳኔ መሰረት ፈቃድ መውሰድ ይችላሉ (ተቃራኒው ካልታዘዘ በስተቀር)።

  የአውቶቡስ ሾፌሮች/ተቆጣጣሪዎች ከመደበኛው ጊዜ ከአንድ/ሁለት ሰዓት (እንዳስፈላጊነቱ) ቀደም ብለው የከሰዓት ስራ ይጀምራሉ።


  ትምህርት ቤቶች እና አስተዳደራዊ መስሪያ ቤቶች መዘጋት

  ሁሉም የትምህርት ቤት ውስጥ ወይም በትምህርት ቤት ንብረት ላይ ያሉ እንቅስቃሴዎች ተሰርዘዋል። ሁሉም የድንገተኛ ሰራተኞች፣ የህንፃ መሃንዲሶችን፣ የፅዳት ሰራተኞችን፣ የጥገና ቦታ ሰራተኞችን እና የጥበቃ ሰራተኞችን ጨምሮ ለስራ ማመልከት ኣለባቸው።


  ትምህርት ቤት ሲዘጋ፣ የአስተዳደር ጽ/ቤቶች ሲከፈቱ

  በትምህርት ቤትም ሆነ በትምህርት ቤት ንብረት ላይ ያሉ ሁሉም እንቅስቃሴዎች ለዛሬ ተሰርዘዋል። የድንገተኛ ሰራተኞች ለስራ ማመልከት ኣለባቸው። ሁሉም የ12- ወራት ሰራተኞች ለስራ ማመልከት ኣለባቸው፣ ሆኖም ሊበራል መቅረት ስራ ላይ ይውላል። የድንገተኛ ሰራተኞች ለስራ ማመልከት ኣለባቸው።