የኤ.ሲ.ፒ.ኤስ. ቨርችዋል ፕለስ+ የትምህርት ቀን እና ከትምህርት በኋላ ፕሮግራም በተደጋጋሚ የሚቀርቡ ጥያቄዋች

FAQ
 • በተደጋጋሚ የሚቀርቡ ጥያቄዋች

   

   አሁን የተመዘገቡ ተማሪዋች በታይትል (Title I)
   የቨርችዋል ፕለስ የትምህርት ቀን እና ከትምህርት በኋላ ፕሮግራም

   በድብልቅ(Hybrid) የትምህርት አሰጣጥ ወቅት

   

  ኤ.ሲ.ፒ.ኤስ. ወደ ድብልቅ(Hybrid) የትምህርት አሰጣጥ ዘዴ በሚሸጋገርበት ወቅት በድብልቅ(Hybrid) የትምህርት አሰጣጥ በት/ቤት በሳምንት ሁለት ቀናት ለመከታተል ለመረጡ የተወሰኑ ተማሪዋችን  በሚከተለው መንገድ ያከናወናል፤

  ማስታወሻ፤  ሁሉም የሽግግር  ሂደት በሰራተኞች  ምደባ፣ በህንፃ የማስተናገድ አቅም የኮሚዪኒቲ  ጤና ሁኔታ መስፈርት እና የውሳኔ መስጫ መስፈርት አመልካቶች ላይ የተመሰረተ ይሆናል።

  • ማክሰኞ፣ ማርች 2 የድብልቅ ፕሮግራም የመረጡ ተማሪዋች K-5 በከተማ አቀፍ ፕሮግራም ልዪ ትምህርት በራሱን የቻለ የሙሉ ቀን ፕሮግራም አገልግሎቶች የሚያገኙ፣ በK-5 ልዪ ትምህርት በንባብ እና በሂሳብ ትምህርት አገልግሎቶች በራሱን የቻለ የሚከታተሉ፣ የመዋእለ ህፃናት የልዩ ትምህርት አገልግሎቶች ተማሪዋች እና K-5 ክፍል  የእንግሊዘኛ ቋንቋ ተማሪዋች አገልግሎት (EL) ተማሪዋች ያካትታል።
  • ማክሰኞ፣ ማርች 9 የድብልቅ ፕሮግራም የመረጡ ከ6-12 ተማሪዋች  የSPED  የከተማአቀፍ እና ራሱን ያቻለ የንባብ እና የሂሳብ ትምህርት የሚከታተሉ እና አዲስ የኢ.ኤል (EL) የ6-12 ተማሪዋች ።
  • ማክሰኞ፣ ማርች 16 የድብልቅ ፕሮግራም የመረጡ ሁሉም ቀሪ  ከመዋእለ ህፃናት - 12 ኛ ክፍል ተማሪዋች ።

  የኤ.ሲ.ፒ.ኤስ. ቨርችዋል ፕለስ+ የትምህርት ቀን እና ከትምህርት በኋላ ፕሮግራም በተመረጡ ቦታዋች በነፃ የታይትል I ተማሪዋችን ለመቆጣጣር ለማቆየት የሚያስችል በድብልቅ ፕሮግራም እንዲቀጥል ይደረጋል።  በአሁኑ ወቅት ተመዘግበው እና በቨርችዋል ፕለስ ፕሮግራም የሚማሩ ተማሪዋች  በቀጣይነት እንዲከታተሉ ይደረጋል።  ለተጨማሪ መረጃ እባክዎን በተደጋጋሚ የሚቀርቡ ጥያቄዋች ይመልከቱ።

   

  ...ኤስ.  ቨርችዋል ፕለስ የትምህርት ቀን እና ከትምህርት በኋላ ፕሮግራም  በተመለከተ               በተደጋጋሚ የሚቀርቡ ጥያቄዋች

  1. የኤ...ኤስ. ቨርችዋል ፕለስ+ የትምህርት ቀን እና ከትምህርት በኋላ ፕሮግራም በድብልቅ ሞዴል የሚቀጥለው እንዴት ነው?

  የኤ.ሲ.ፒ.ኤስ. ቨርችዋል ፕለስ+ የትምህርት ቀን እና ከትምህርት በኋላ ፕሮግራም አሁን ባለበት ቦታ ይቀጥላል በተመሳሳይ መልኩ እና አገልግሎት በሚከተሉት ቦታዋች ይካሄዳል፤

  • የወንዶችን ሴት ልጆች ክለብ (401 N. Payne -22314)
  • ቺክ አርምስትሮንግ መዝናኛ ማእከል (25 W. Reed – 22305)
  • ፓትሪክ ሄንሪ መዝናኛ ማእከል (4653 Taney Ave. - 22304
  • ሣሚኤል ተከር አንደኛ ደረጃ ት/ቤት/ YMCA ፕሮግራም (435 Ferdinand Day Dr. – 22304)
  • ዊሊያም ራምሴ የመዝናኛ ማእከል (5650 Sanger Ave. - 22311

  ሰዓቱና የሚሰጠው አገልግሎት አንድ ዓይነት ቢሆንም የሚከተሉት የኤ.ሲ.ፒ.ኤስ. ቨርችዋል ፕለስ ቦታዋች የሚከተሉት ቦታዋች ላይ ለውጥ ይኖራል፤

  አሁኑ ካሉበት ቦታ፤  ጄምስ ኬ. ፖልክ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት፤ (5000 Polk Ave. – 22304)

  ወደ አዲሱ ቦታ፤   ኤ.ሲ.ፒ.ኤስ. ቨርችዋል ፕለስ+ የትምህርት ቀን እና ከትምህርት በኋላ ፕሮግራም  ከጄምስ ኬ. ፖልክ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት፤ ወደ ፈርዲናድ ዴይ አንደኛ ደረጃ /ቤት  (1701 N. Beauregard - 22311)  ይዛወራል በፈርዲናድ ቲ ዴይ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት በፕሮግራሙ የሚሳተፉ  ተማሪዋችን በተሻለ ለማስተናገድ።  *  ለፈርዲናድ ቲ. ዴይ ተማሪዋች ሰኞ፣ ማርች 1 በሁለቱም ቦታዋች ፕሮግራም አይካሄደም።  በፈርዲናድ ቲ. ዴይ ፕሮግራም የሚጀመረው ማክሰኞ፣ ማርች 2 ነው።

  1. የእኔ ተማሪ በድብልቅ ፕሮግራም የማይከታተል ሆኖም ግን በቨርችዋል ትምህርት የሚከታተል ክሆነ እርሱ/ አሁን በተመዘገቡበት የኤ...ኤስ. ቨርችዋል ፕለስ+ የትምህርት ቀን እና ከትምህርት በኋላ ፕሮግራም መቀጠል ይችላሉ?

  አዎ። ቤተሰቦቻቸው በቨርችዋል ትምህርት እንዲከታተሉ የመረጡላቸው ተማሪዋች በቨርችዋል ፕለስ የትምህርት ቀን እና ከትምህርት በኋላ ፕሮግራም ቦታ በሳምንት አምስት ቀን መከታተል ሊቀጥሉ ይችላሉ።  ወደ ቦታ የሚያደርስ የትራንስፖርት አገልግሎት አይሰጥም።  ወላጅ/ አሳዳጊ የትራንስፓርት አገልግሎት መስጠት ይኖርባቸዋል።  የአገልግሎት ሰዓት እና ዓይነት እንደነበረው ይቀጥላል።

  1. የእኔ ተማሪ የድብልቅ ፕሮግራም በትምህርት ቤታቸው የሚከታተሉ ከሆነ እርሱ/ የኤ...ኤስ. ቨርችዋል ፕለስ+ የሚሰጠውን የትምህርት ቀን እና ከትምህርት በኋላ ፕሮግራም በድብልቅ ፕሮግራም በማይሰጠበት ወቅት መከታተል ይቻላሉ?

  አዎ። በእነዚህ ፕሮግራሞች አገልግሎት የሚያገኙ  የድብልቅ ሞዲል የመረጡ ተማሪዋች  የድብልቅ ትምህርት በማይሰጠበት ቀናት  በተመዘገቡበት የቨርችዋል ፕላስ + የትምህርት ቀን እና ከትምህርት በኋላ መከታተያ  ቦታ መማር ይችላሉ።  ወደ ቦታ የሚያደርስ የትራንስፖርት አገልግሎት አይሰጥም። በእነዚህ ቀናት ወላጅ/ አሳዳጊ የትራንስፓርት አገልግሎት መስጠት ይኖርባቸዋል። የአገልግሎት ሰዓት እና ዓይነት እንደነበረው ይቀጥላል።

  1. የድብልቅ ፕሮግራም ተማሪዋች ፕሮግራሙ በማይሰጥባቸው ቀናት የቨርችዋል ፕለስ+ የትምህርት ቀን የማቆያ ፕሮግራም/ቦታ የሚወሰድ የትራንስፓርት አገልግሎት ሊያገኙ ይችላሉ።

  አይ። የኤ.ሲ.ፒ.ኤስ. ተማሪዋች ወደ ትምህርት ቤት ለማመላልስ አገልግሎት የሚሰጥ ቢሆንም የድብልቅ የትምህርት ፕሮግራም በማይኖርበት ቀን ምንም የትራንስፓርት አገልግሎት አይኖርም።  ወላጅ/ አሳዳጊ  የድብልቅ ፕሮራሙ በማይኖርበት ቀናት  ልጆቻቸውን ወደ ቨርችዋል ፕለስ ፕሮግራም/ቦታ ማመላለስ መቀጠል ይኖርባቸዋል።

  1. በድብልቅ የትምህርት ቀናት ከትምህርት በኋላ ፕሮግራም እንዴት ይሆናል? የእኔ ልጅ በአካል በመገኘት በድብልቅ ፕሮግራም ትምህርት ከተከታተለ በኋላ የኤ...ኤስ. የቨርችዋል ፕለስ ፕሮግራም መክታተል ይችላል ?

  እንደሁኔታው ነው።

  በሚከተሉት ትምህርት ቤቶች  የሚማሩ ተማሪዋች ከድብልቅ የትምህርት ቀን በኋላ በቅርብ ወደአለው ትምህርት ቤት  ወይም በቅርብ ወደሚገኘው የቨርችዋል ፕለስ ቦታዋች በእግር ሊሄዱ ይችላሉ።

  • በወላጆች/አሳዳጊዋች ፍቃድ ፤ የኮራ ኬሊ አንደኛ ደረጃ /ቤት ተማሪዋች በአሁኑ ወቅት  በቸክ አርምስትሮንግ መዝናኛ ማእከል የቨርችዋል ፕለስ+ ፕሮግራም የሚከታተሉ የድብልቅ  ትምህርቱ ካለቀ በኋላ በእግራቸው ወደ መዝናኛ ማእከሉ መሄድ ይችላሉ።  ልጅዎ  ከድብልቅ ትምህርት በኋላ ወደ ዚያ እንደሚመጣ እንዲያውቁ ለማድረግ እባክዎን  ከመዝናኛ ማእከሉ ሰራተኞች ይነጋገሩ።
  • በወላጆች/አሳዳጊዋች ፍቃድ ፤ የፈርዲናድ . ዴይ አንደኛ ደረጃ /ቤት ተማሪዋች በአሁኑ ወቅት በጄምስ ኬ. ፖልክ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት የቨርችዋል ፕለስ+ ፕሮግራም የሚከታተሉ (ከማርች 1፣ 2021 ጀምሮ ወደ ፈርዲናድ ቲ. ዴይ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት እንዲዛወር ተደርጎል።) የድብልቅ  ትምህርቱ ካለቀ በኋላ  በፈርዲናድ ቲ. ዴይ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ፕሮግራሙን መከታተል ይችላሉ ።  ልጅዎ  ከድብልቅ ትምህርት በኋላ ወደ ዚያ እንደሚመጣ እንዲያውቁ ለማድረግ እባክዎን  ከሰራተኞች ጋር ይነጋገሩ።
  • በወላጆች/አሳዳጊዋች ፍቃድየጀፈርሰን ሂውስተን /ቤት ተማሪዋች በአሁኑ ወቅት  በወንዶችና በሴቶች ክለብ  የቨርችዋል ፕለስ+ ፕሮግራም የሚከታተሉ የድብልቅ  ትምህርቱ ካለቀ በኋላ በእግራቸው ወደ ክለቡ መሄድ ይችላሉ። ልጅዎ  ከድብልቅ ትምህርት በኋላ ወደ ዚያ እንደሚመጣ እንዲያውቁ ለማድረግ እባክዎን  ከክለቡ ሰራተኞች ይነጋገሩ።
  • በወላጆች/አሳዳጊዋች ፍቃድየፓትሪክ ሄንሪ መዝናኛ /ቤት ተማሪዋች  በአሁኑ ወቅት  በፓትሪክ ሄንሪ መዝናኛ ማእከል የቨርችዋል ፕለስ+ ፕሮግራም የሚከታተሉ የድብልቅ  ትምህርቱ ካለቀ በኋላ በእግራቸው ወደ መዝናኛ ማእከሉ መሄድ ይችላሉ። ልጅዎ  ከድብልቅ ትምህርት በኋላ ወደ ዚያ እንደሚመጣ እንዲያውቁ ለማድረግ እባክዎን  ከመዝናኛ ማእከል ሰራተኞች ጋር ይነጋገሩ።
  • በወላጆች/አሳዳጊዋች ፍቃድየዊሊያም ራምሴ አንደኛ ደረጃ /ቤት ተማሪዋች  በአሁኑ ወቅት  በዊሊያም ራምሴ የመዝናኛ ማእከል  የቨርችዋል ፕለስ+ ፕሮግራም የሚከታተሉ የድብልቅ  ትምህርቱ ካለቀ በኋላ በእግራቸው ወደ መዝናኛ ማእከሉ መሄድ ይችላሉ። ልጅዎ  ከድብልቅ ትምህርት በኋላ ወደ ዚያ እንደሚመጣ እንዲያውቁ ለማድረግ እባክዎን  ከመዝናኛ ማእከል ሰራተኞች ጋር ይነጋገሩ።

    ከላይ ከተጠቀሱት ውጭ በሌሎች ትምህርት ቤቶች ተማሪዋች የሚመሩ ከሆነ በቨርችዋል ፕለስ ፕሮግራም ከትምህርት በኋላ ፕሮግራም መከታተል የሚችሉት  ከትምህርት በኋላ ፕሮግራም ወደ አለበት ቦታ ወላጅ/ አሳዳጊ ልጆቻቸውን የሚወስዶቸው ከሆነ ብቻ ነው።   ስለአሉት አማራጮች ለመወያየት  ከኤ.ሲ.ፒ.ኤስ. የቨርችዋል  ፕለስ ፕሮግራም ሰራተኞች  ጋር ይነጋገሩ።

  1. የሙሉ ቀን የልጅ ጥበቃ አገልግሎት የምፈልግ እና ልጄን ከድብልቅ ትምህርት በኋላ ለማመላለስ የማልችል ከሆነስ?

   የድብልቅ ትምህርት ቀደም ሲል  የመረጡ  ወላጆች በቨርችዋል በ100% የማስተማር እድል መምረጥ ይችላሉ። ስለሆነም ልጅዎ የኤ.ሲ.ፒ.ኤስ. ቨርችዋል ትምህርት ፕሮግራም በሳምንት አምስት ቀናት መከታተል ይችላል ።  የራስዎ ቤተሰብ ፍላጎት ይህን መቀየር ከሆነ እባክዎን ትምህርት ቤትዎ ጋር ይገናኙ ከድብልቅ ፕሮግራም ወደ ቨርችዋል ሞዴል ለመቀየር።  ከቨርችዋል ፕለስ ፕሮግራም/ቦታ ሰራተኞች  ለልጅዎ አምስት ቀን በሙሉ እንዲከታተል ተገቢውን ዝግጅት እንዲያደርጉ ከእነርሱ ጋር ይነጋገሩ ።

  1. በአሁኑ ወቅት የኤ...ኤስ. ቨርችዋል ፕለስ+ የትምህርት ቀን እና ከትምህርት በኋላ ፕሮግራም የማይሳተፉ ተጨማሪ ተማሪዋችን ለመቀበል ክፍት ቦታ ይኖራል?

  እርስዎ ወይም ሌላ ሰው የሚያውቁት ልጃቸውን ማስመዝገብ የሚፈልጉ ካሉ እባክዎን በትምህርት ቤት ያሉትን የወላጅ አገናኝ  ጋር ይገናኙ ተማሪዋቹ ምደባ የሚያገኙበትን ሁኔታ ለመወሰን  ከሚመለለከታቸው ሰራተኞች ጋር ግንኙነት ያደርጋሉ። ወይም በኤ.ሲ.ፒ.ኤስ. የድጋፍ መስጫ የስልክ መስመር ላይ ይደውሉ፤  

  ለእንግሊዘኛ፤ 703-844-1763 ይደውሉ ወይም ቴክስት ያድርጉ

  ለስፓኒሽ፤ 703-844-3424 ይደውሉ ወይም ቴክስት ያድርጉ

  ለአማርኛ፤ 703-927-6866 ይደውሉ ወይም ቴክስት ያድርጉ

  ለአረብኛ፤ 703-927-7095 ይደውሉ ወይም ቴክስት ያድርጉ

  ተጨማሪ የልጅ ጥበቃ አገልግሎት የሚሰጡ ለማወቅ በተጨማሪ ይህን ይመልከቱ፤  ACPS Child Care Webpage

  1. ልጄ አሁን በመከታተል ላይ ስላለው ስለኤ...ኤስ. ቨርችዋል ፕለስ+ የትምህርት ቀን እና ከትምህርት በኋላ ፕሮግራም ተጨማሪ ጥያቄዋች ካለኝስ?

  ተጨማሪ ጥያቄዋች ካላዋት  በኤ.ሲ.ፒ.ኤስ. ቨርችዋል ፕለስ ፕሮግራም/ቦታ አሁን ልጅዎ በሚከታተልበት  ከቦታው አስተባባሪ ጋር  እባክዎን ይነጋገሩ።