ለአማርኛ ተናጋሪዎች የቀረበ መረጃ (Information for Amharic Speakers)

 • በዚህኛው የACPS ድረ ገጽ ክፍል ወሳኝ የሆኑ በባለሙያ ወደ አማርኛ የተተረጎሙ የ ACPS መረጃዎችን ያገኛሉ።

  እንደ አማራጭም በዚህ ድረ ገጽ ላይ ወይም የሌሎች የትምህርት ቤት ድረ ገጾችን ለመተርጎም Google Translate መጠቀም ይችላሉ። በማንኛውም ገጽ አናት ላይ 'More' የሚለውን በመንካት ወደታች ከሚመጣው ዝርዝር ውስጥ ቋንቋዎን ይምረጡ። Google Translate የሚሰጠው ትርጉም በኮምፒውተር የተተረጎመ ስለሆነ ፍጹም ትክክል ላይሆን ይችላል፣ ነገር ግን ድረ ገጹን በተሻለ ለመጠቀም በቂ መረጃ ሊሰጥዎ ይችላል።

  በትምህርት ቤትዎ ውስጥ በአማርኛ እገዛ ያግኙ፦ የትርጉም እና የአስተርጓሚ አገልግሎቶች ለ ACPS ቤተሰቦች ይገኛሉ (PDF)

  የድንገተኛ ጊዜ ማስታወቂያዎችን እና ህትመቶቸችን በአማርኛ ማግኘት ይችላሉ

  በአማርኛ መረጃዎችን እንደሚያገኙ ለማረጋገጥ የትምህርት ቤትዎ ሬጂስትራር በልጅዎ PowerSchool መዝገብ ላይ ያለውን “የሚመርጡት የግንኙነት ቋንቋ” ወቅቱን የጠበቀ አድርገው እንዲያስቀምጡ ይንገሩ። ACPS በተቻለ መጠን የድንገተኛ ጊዜ ማስጠንቀቂያዎችን እና ህትመቶችን ለማስተርጎም ጥረት ያደርጋል።

  የጽሁፍ መልዕክቶች/ቴክስቶች በአማርኛ

  ከACPS መረጃን በአማርኛ በስልክዎ ለማግኘት @amharic ብለው ወደ ስልክ ቁጥር 81010 ይላኩ።